Amharic, 2007

Welcome to your Amharic, 2007



የአማርኛ ፈተና ጥያቄ ስኔ 2007 ዓ.ም



መመሪያ አንድ፡- ከጥያቄ 1 እስከ 12 ድረስ የቀረቡት ጥያቄዎች ክፍል እንድ ቀጥሉ በቀረበው ምንባብ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ከተሰጡት አማራጮች መካከል በምንባቡ መሠረት ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡



ምንባብ

የአሸንዳ ጭፈራ የአሸንዳ ጭፈራ ከነሐሴ 16 እስከ 19 ባሉ ሦስት ተከታታይ ቀናት ይከበራል፡፡ ትዳር የመሠረተች በአሸንዳ ጭፈራ እትሳተፍም፡፡ በዓሉ የመስክ በዓል በመሆኑ የአሸንዳ ሴቶች የት ወላችሁ ተብለው የማይጠየቁበት የነፃነት ቀናቸው ነው፡፡ በአሸንዳ ፍቅራቸውን የሚገልፁበት፣ መንደሮቻቸውን የሚያደምቁበት፤ አባቶቻቸውን እና እናቶቻቸውን የሚያከብሩበት ህዝባዊ በዓል ነው፡፡

ለበዓሉ ውስን ቀናቶች ሲቀሩ ሌቶች ቡድን ይመሠርታሉ፡፡ ቡድኑ በአብሮ አደግ ልጃገረዶች የአንድ መንደር ልጆች ይገተራል፡፡ እነዚህ አብሮ አደጎችን ሴራ-ሚዜ ይባለሉ፡፡ በቡድነም የቡድን መሪ፣ ዘፈን አውጪ፣ ከበሮ መቺ በሚል ይደራጃሉ፡፡ የቡድን መሪዋ ጥና ተግባር በድነን በተገቢው መምራት፤ ዘፈን የሚያወጡ! ከበሮ የሚመቱ መደልደል፣ ከየቤቱ የሚሰጡ ስጦታዎችን የመያዝ ሥራዎችን ታከናውናለች፡፡ ሴራሚዜዎቹ የሚወጡ ዘፈኖች ይቀበላሉ፡፡ ቡድኑን ያነቃቃሉ፡፡ የቡድኑ አባላት በዓሉ ሊደምር ቀናቶች ሲቀሩ ለበዓሉ ድምቀት የሚሰጡ የሴቶች መጋጌጫዎች እንደከል፡ በዳሌያቸው የሚያስሩት አሸንድየ በመቁረጥና እንሶስላ በማዘጋጀት ዝግጅቱ ይጀመራል።

በበዓሉ ቀንም ኣሳዲዎች (ኮረዳዎቹ) ፀጉራቸውን ቅቤ ተቀብተው እንሶስላቸውም ሞቀው በኩላቸው ደምቀው፣ በአገር ባህል ልብሳቸው አሽብርቀው፣ በዳሌያቸው ዙሪያ አሸንድየ አስረው ከበሮዋቸውን እየመቱ በገላጣ ሜዳ ላይ ይሰበስባሉ፡፡ የበዓሉ መጀመሪያ ቀን በአቅራቢያቸው በሚገኝ ቤተ-ክርስቲያን በመሄድ ለፈጣሪያቸው ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ በመቀጠልም አምና የቡድኑ አባል የነበረች ነገር ግን ዘንድሮ ባለትዳር የሆነችው ጓደኛቸውቤት በመሄድ የአሸንዳ ጭፈራቸውን ያሣያሉ፡፡ ጓደኛቸውን ያወዱሷታል። ትዳሯ ያማረ፣ ዘሯ የተባረከ እንዲሆን በዜማና ግጥማቸው ይመኙላታል፡፡ መሽራዋም ሚዜዎቿ እንደሚመጡ ስለምታውቅ ቀድማ የሚበላ ነገር ታዘጋጃለች፡፡ ያዘጋጀችውንም ምግብ እንዲመገቡ ታደትጋለች፡፡ በመቀጠልም ስጦታ ትሰጣቸዋለች፡፡

የአጀንዳ ቡድን ከሚዜያቸው ቤት አሀዱ ብለው የጀመሩት የአሸንዳ ጭፈራ በየቤቱ በመዞር ለህብረተሰቡ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው በጭፈራቸው ያስተላልፋሉ፡፡ በምላሹም መለስተኛ ስጦታዎች ያገኛሉ፡፡ በዓሉ ለሁለት ቀናት እየተዜመ ይከበራል፡፡ በሁለት ቀናት ውስጥ ከህብተሰቡ የተለያዩ ስጦታዎችን ይሰበስባሉ፡፡ ወንዝ ተሻግረው በየጎጡ ስለሚሩ ወንዶችም" ያጅቧቸዋል፡፡ ከጥቃትም ይጠብቋቸዋል፡፡ በሦስተኛው ቀን ሁሉም የመንደሩ የአሸንዳ ቡድኖች በአንድ ላይ በመስብሰብ ነፃ የጭፈራ ቀን ያከብራሉ፡፡ ጭፈራውም በወንዝ ዳር ባሉ እዳ (ዋርካ) ዛፍ ስር ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ለከርሞ በሰላም እንዲያገናኛቸው ተመኝተው በዓሉን በድምቀት ይሸኙታል፡፡

ምንጭ፡- ክብሮም አሰፋ ሞላ፡፡ 2005 ዓ.ም የራያ ሕዝብ ባህልና ታሪክ፡፡ እእ.፣ፋር ኢስት ማተሚያ ቤት ከገጽ 137-140 በመጠኑ ተሻሽሉ የተወሰደ

1. 
በአሸንዳ በዓል በዋናነት የሚሣተፉት እነማን ናቸው?

2. 
የአሸንዳ በዓል የመስክ በዓል ነው ሲባል ምን ማለት ነው?

3. 
በአሸንዳ በዓል የቡድን መሳሪዋ ተግባር ምንድን ነው?

4. 
ሴራሚዜ የሚባሉት እነማን ናቸው?

5. 
የአሸንዳ በዓል ተሣታፊዎች አሸንድየን የሚያስሩት ምናቸው ላይ ነው?

6. 
እንሶስላ_____:: ክፍት ቦታው በትክክል የሚያሟላው የትኛው ነው?

7. 
አሸንዳ በዓል ሥርዓታዊ የአካባበር ቅደም ተከተል አለው፡፡ የሚከተሉት መካከል ትክክልኛውን ቅደም ተከተል የያዘው የትኛው ነው?

8. 
በአሸንዳ በዐል የወንዶች ሚና ምንድነው?

9. 
የአሸንዳ በዓል ለስንት ቀን (ቀናት) ይከበራል?

10. 
የአሸንዳ በዓል ለአሸንዳ ሴቶች የነፃነት ቀናቸው ነው የተባለው ለምንድነው?

11. 
አሳዲ ለሚለው ቃል ፍቺ ለሆን የሚችለው ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው?

12. 
የምንባቡ ይዘት ከሚከተሉት መካከል የትኛው ያንፀባርቃል?

ክፍል ሁለት
መመሪያ ሁለት :- ከጥያቂ 13 እስከ 29 ድረስ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ከቀረቡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።

13. 
ከሚከተሉት አረፍተ ነገሮች መካከል በእርግጠኝነት የሚደመድመው የትኛው ነው?

14. 
“ያልጠረጠረ ተመነጠረ" በሚለው ሃምሣሌያዊ አነጋገር መንስኤ የሆነው ድርጊት የትኛው ነው?

15. 
እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝ ማለትን ያስከትላል። በሚል እረፍት ነገር ውስጥ ለድርጊቱ ውጤት የሆነው የቱ ነው?

16. 
ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ቅደም ተከተሉን የጠበቀ የድርጊት መመሪያ የትኛው ነው?

17. 
ከሚከተሉት አማራጮች መካከል በሥርዓት መመራትን የግድ የሚል የትኛው ነው?

18. 
ከሚከተሉት አማራጮች መካከል የንባብ ፍጥነትን የሚቀንስ የትኛው ነው?

19. 
ከሚከተሉት መካከል ስለንባብ ትክክል የሆነው የትኛው ነው?

20. 
ከሚከተሉት ከትንሽ ወደ ብዙ በሚል ቅደም ተከተል የተፃፈው የትኛው ነው?

21. 
ከሚከተሉት ምሣሌያዊ አነጋገሮች መካከል ብልህነትን የሚያወድስ የትኛው

22. 
ከሚከተሉት መካከል የባስ ነገር ማጋጠሙን የሚያመላክተው ምሣሌያዊ አነጋገር የትኛው ነው?

23. 
ከ ቋንቋ ክሂሎች መካከል ቀዳማይ የሆነው ዘርፍ የትኛው ነው?

24. 
የንግግር ችሎታን አዳብሮ ሰዎችን ለማሳመን ከሚከተሉት በየትኞቹ በቂ ልምምድ ማድረግ ያስፈልጋል?

25. 
“በጥራት ማምረት ትርፋማነትን ሲያስገኝ ይህም በኢኮኖሚ መበልፀግን ያመጣል” በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ በመንስኤነት ሊጠቀሱ የሚችሉት የትኞቹ ናቸው?

26. 
ከዚህ በታች የተፃፉት አረፍተ ነገቶች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው ቢፃፉ አንድ አንቀጽ ይወጣቸዋል፡፡ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን ቅደም ተከተል የሚያሳየው የትኛው ነው?

  1. ይህ ጥናት አንድ ሰው አንድ ተግባር ሲያከናውን የእጅ እንቅስቃሴ እያንዳዱን ክንውን ለመጨረስ ስንት ሴከንዶች እንደሚወስድ ያሳያል።
  2. አነዚህ ባልና ሚስት ተመራማሪዎች የሚታወቁት በጊዜና እንቅስቃሴ ጥናት ነው፡፡
  3. ብርዜና አቶምሣ ባልና ሚስት የነበሩ ተመራማሪዎች ናቸው፡፡
  4. ባልና ሚስቶች ሕይወታቸውን በሙሉ ያለፉት የዚህ ዓይነት ቀልጣፍ የአሠራር መንገድ ለመፈለግ ነው፡፡

27. 
ከሚከተሉት ምሣሌያዊ አነጋገሮች መካከል አፍራሽ የሆነው የትኛው ነው?

28. 
ከሚከተሉት ሥነ-ቃሎች መካከል እንቆቅልሽ የሆነው የትኛው ነው?

ክፍል ሦስት
መመሪያ ሦስት፡- ከጥያቂ 30 እስከ 38 ድረስ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ከቀረቡት አማራጮች መከካል ትክክለኛውን ምረጡ፡፡

29. 
አወቀ፣ዕውቀት ብለን “ዐዋዊ' ብንል በለጠ፣ ብልጠት ብለን____ እንላለን፡፡

30. 
“አንተ የምነግርህን አይሰማም፡፡” በዚህ አረፍተ ነገር ውስጥ የሚታየው ስህተት ምንድነው?

31. 
ከሚከተሉት አረፍተ ነገሮች መካከል ትክክለኛ የአያያዥ ቃል አጠቃቀም የሚታይበት የትኛው ነው?

32. 
“የልጁ ጠባይ በጣም አስቸጋሪ ነው_____መመለስ አለብን፡፡”

33. 
“ኢ.ፌ.ዲ.ሪ” በሚል ምህፃረ ቃል ተዘርዝሮ ቢጻፍ ትክክል የሚሆነው የትኛው ነው?

34. 
“በጧት ገበያ የሄድኩት አዲስ ልብስ ነበር ለመግዛት

ልብስ ካገኘሁ በጥቂት

ሁሉንም በተውሁት”

በሚለው ግጥም ውስጥ የተሠመረበት ቀን “ማስተዋል” የሚለውን ትርጉም የሚያስገኘው እንዴት ዋው ሲነበብ ነው፡፡

35. 
ከሚከተሉት አረፍተ ነገሮች መካከል ጥምር ቃል የያዘው የትኛው ነው?

36. 
“ነት” የሚለው ቅጥያ ተጨምሮበት የሚታየው በየትኛው ቃል ላይ ነው?

37. 
“ችኩል መንገደኛ ካሰበበት ቦታ አይደርስም” በሚለው አረፍተ ነገር ውስጥ የስም ገላጭ ሆኖ የገባው ቃል የትኛው ነው?

38. 
“ጠፋ” የሚለው ቃል “ወደመ” የሚለውን ትርጉም በየትኛው አረፍተ ነገር ባለው አገባብ ውስጥ ነው?

39. 
“መጠምዘዝ፣ አጠመዛዘዝ ብሎ ጥምዝ ቢል “መደለዝ፣ አደላለዝ" ብሎ ምን ይላል?

40. 
“ዝግ” የሚለው ቃል ጠብቆ የሚነበበው በየትኛው አረፍተ ነገር ውስጥ ነው?

41. 
ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ከሌሎች ጋር በፍቺ የማይመሳስለው ቃል የትኛው ነው?

42. 
“አመርሽ” የሚለው ቃል “አንቺ” የሚለውን በባለቤትነት ከወሰደ “አመርን” የሚለው ቃል ከሚከተሉት የትኛውን ይውሰድ?

43. 
ከሚከተሉት ቃላት መካከል የድምፅ መዋጥ የሚታይበት የትኛው ነው?

44. 
ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ባህላዊ የቡና አፈላልን የድርጊት ቅደም ተከተል የያዘው የትኛው ነው?

45. 
”ማር ቀምሼ አላውቅም እኔ ወንድማችሁ

ያገሬ ወጣቶች ተማሩ እባካችሁ።”

በሚለው ግጥም ውስጥ ሁለት የተለያዩ ትርጉሞች የያዘው ቃል የትኛው ነው?

46. 

47. 
“ሣቅ በሁለት ሰዎች መካከል ያለውን ወስን ይሰብራል፡፡ አስፈላጊ ጭንቀቶችን ያረግባል፡፡ ፈገግታን ይፈጥራል፡፡ ችግሮችን ይቋቋማል፡፡” የዚህ ጽሑፍ ዋና ሐሣብ የተገለፀው በየትኛው አማራጭ ነው?

48. 
“የንባብ ባህል ባልዳበረበት ሁኔታ ውስጥ ሆነን ምጣኔ ሀብት፣ ዕድገትን መሻት ተላላነት ነው፡፡” የሚለው ሐሣብ ከሚካተሉት አማራጮች መካከል ከየትኛው ጋር ይመሳሰላል?

49. 
በአንድ በተለመደ ሰዓት ምንም ይሁን ምን መመገብ እንደሚያስፈልግ የሚገልፀው አባባል ከሚከተሉት መነ የትኛው ነው?

50. 
በአንድ ጽሑፍ ውስጥ ቦታና ጊዜ፣ የተገኙና ያልተገኙ አባላት ስምና አጀንዳ ተፅፎ ከተገኘ ያንን ጽሑፍ ምን ብሎ መጥራት ይቻላል?

51. 
ተዘበራርቀው የተቀመጡትን የሚከተሉትን አረፍተ ነገሮች በቅደም ተከተል የያዘው አማራጭ የትኛው ነው?

  1. መካሻ ዛሬ በሕይወት የልም፡፡
  2. መካሻ በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ፡፡
  3. በመቀጠል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ
  4. ከዚያም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የአንድ ዓመት የመምህርነት ግዳጅን ተወጣ፡፡
  5. ዕደሜው ለትምህርት ሲደርስ ትምህርት ቤት ገብቶ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ከመምህራን ሥልጠና ጋር አጠናቀቀ፡፡

52. 
ከላይ በተራ ቁጥር 51 በቅደም ተከተል እንዲቀመጥ የተደረገው ሐሣብ ምን ላይ ያተኩራል

53. 
በሚከተሉት ተዘበራርቀው የተቀመጡት አረፍተ ነገሮች በየትኛው ቅደም ተከተል ቢቀመጡ የተቃና አንቀጽ ይፈጥራሉ?

  1. በዚህ ቀጥሉ ጥሩ ጥሩ ድንጋዮች እንዳይነቃነቁ ተደርገው ተርታውን በተቆፈረው ቦታ ውስጥ ይቆማሉ፡፡
  2. የቤት መሠረት የሚያርፍበት ቦታ በሃምሣ ሴንቲ ስፋት ይቆፈራል።
  3. ከዚያም የተረበረበው ድንጋይ እንዲጠነክር አሽዋና ሲሚንቶ ተቀላቅሎ ከተቦካ በኋላ ይደረግበታል፡፡
  4. በመቀጠል ኮረትና አነስተኛ ድንጋዮች በቆመት ድንጋዮች መካከል የሚታዩትን ቀዳዳዎች እንዲደፍነ ይደጋል፡፡

54. 
የመስሪያ ቤት ደብዳቤ የሚዛቸው በየትኛው አማራጭ ውስጥ ያሉትን ነጥቦች ነው?

55. 
ከዚህ በታች የተፃፈው ኣንቀጽ ከተሰጡት አማራጮች መካከል ለየትኛው ምሣሌ ይሆናል?

ኢትዮጵያውያን ከመስከረም እስከ ነሐሴ ያሉትን አሥራ ሁለት ወራት በምክንያታዊ ትርጉም ሲሰይሙ አውሮፓውያን ግን ያመልኳቸው የነበሩትን ጣኦታት መሠረት ያደርጋሉ፡፡ ለምሣሌ ሰኔ የተሰኘው ወር ስኒየ ከሚል ግዕዝ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አማረ ማለት ነው፡፡ የአውሮፓውያን ስድስተኛው ግን ስያሜ ያገኘው ጁኖ ከምትባለው የሠርግ ወይም የጋብቻ አምላክ ነው።

ከጥያቄ 56 እስከ 60 ድረስ ያሉት ጥያቄዎች ቀጥሎ በቀረበው ግጥም ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ግጥሙን በትኩረት ካነበባችሁ በኋላ ለእያንዳንዱ ጥያቄ ከቀረቡት አማራጮች መካከል ተገቢውን መልስ ስጡ፡፡

ዓለሙን ጠፍጥፌው ቂጣ በጋገርሁት

ውሃውን ንጨ ቅቤ ____

ባወጣሁት ቅቤ ቂጣዬን አርሼ

ጨጨብሣ ጭብጦ አድርጌ ለውሼ

አንዴ በገመጥሁት አንጀቴን ባራስሁት

ምኞት ፈረስ ሆኖ የሽምጥ አይሄድም

ደንገላሣ አይመታም ሶምሶማም አይረግጥም

በሕገ ተፈጥሮ በታሪክ ሥራቱ

ዓለም እንደወትሮው ዓለም አንደጥንቱ፡፡

56. 
ከላይ የቀረበው ግጥዎም ከሚከተሉት ሐሣቦች የትኛውን ያጠናክራል?

57. 
ግጥሙ በሰንት ስንኞችና ሐረጎት የተገነባ ነው?

58. 
የግጥሙ ደራሲ በግጥሙ ውስጥ ምኞትን ለመግለጽ በዋናነት የተጠቀመበት ቃል ምንድን ነው?

59. 
ገጣሚው ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው?

60. 
በሁለተኛው ስንኝ በተተወው ባዶ ቦታ ላይ ቢገባ የግጥሙን ሐሣብና ምጣኔ የተሟላ የሚያደርገው ከሚከተሉት የትኛው ነው?

Leave a Reply