Welcome to your ክፍል 3 ግብረ ገብ ምዕራፍ 1
የሚከተሉትን 30 ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።
1.
የሰው ልጆች ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ማሰብ የሚችሉ በመሆናቸው ምን ተብለው ይጠራሉ?
2.
የሰው ልጆች በምን ቢለያዩም በሰብአዊነታቸው ግን እኩል ናቸው?
3.
"የሰው ዋጋ" ማለት ምን ማለት ነው?
4.
ሰዎች ክብራቸውን እንዲያጡ የሚያደርግ መጥፎ ባህሪ የትኛው ነው?
5.
የሌሎችን ስቃይ ለማቅለል ፍላጎት ያለው ጥልቅ ግንዛቤ ምን ይባላል?
6.
የሌሎች ሰዎችን ስሜት መረዳት እና ድጋፍ ማድረግን የሚጨምረው የቱ ነው?
7.
ሰብአዊነት ስለ ሁሉም የሰው ልጆች ምን ማረጋገጫ ይሰጣል?
8.
ሰብአዊ መብት ከየትኛው ጽንሰ ሃሳብ ጋር የማይነጣጠል ነው?
9.
ለአንድ ሰው ወይም ነገር ያለን ጥልቅ የወዳጅነት እና የመተሳሰብ ስሜት ምን ይባላል?
10.
ሰዎች በሰብአዊነታቸው ሳይኮሩ ሲቀሩ ምን ሊያጡ ይችላሉ?
11.
ከልብ የመነጨ መልካምነት እና መተባበር ምን ተብሎ ይገለጻል?
12.
የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጥረታት የሚለየው በምንድን ነው?
13.
ለሰብአዊ እርዳታ መሰረት የሚሆነው የቱ ነው?
14.
ሁሉም የሰው ልጆች ነፃ ሆነው በምን እኩል ሆነው ይወለዳሉ?
15.
ሰዎች እርስ በርስ እንዲግባቡ እና ወዳጅነት እንዲመሰርቱ የሚያስችል ተግባር ምንድን ነው?
16.
የሀገር ወዳድ ሰዎች ባህሪ ምን ይባላል?
17.
በማህበረሰብ ውስጥ ስነ ምግባር የጎደለው ድርጊት መፈጸም ምንን ያስከትላል?
18.
ርህራሄ በሰዎች መካከል ምንን ይገነባል?
19.
ሰብአዊ ክብር በሰዎች ዘንድ እንዲከበር ምን ማድረግ ያስፈልጋል?
20.
የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብሩ ከምን ጋር ፈጽሞ አይለይም?
21.
በአንድ በኩል የሰው ተፈጥሮን በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ባህሪን የሚያመለክተው ምንድን ነው?
22.
የሰው ልጆች በተፈጥሯቸው ሰብዓዊ ክብር ያላቸው በመሆኑ እርስ በርሳቸው በምን መንፈስ መተጋገዝ አለባቸው?
23.
ለተቸገሩ ሰዎች ያለ ክፍያ ወይም በነፃ የሆነ ነገር መስጠት ምን ይባላል?
24.
የሰብአዊነት መገለጫ የሆነውና ለአንድ ሰው ጥልቅ የሆነ ስሜታዊ ቅርርብ መመሥረትን የሚጨምረው የቱ ነው?
25.
የሰው ልጅ ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ማሰብ የሚችል መሆኑን የሚያሳየው የቱ ነው?
26.
ሰዎች ለራሳቸው ጥሩ ግምት ካልሰጡ ምን ሊያጡ ይችላሉ?
27.
የሰብአዊ መብት ህጎች ሁሉም የሰው ልጆች እንዴት እንደሚወለዱ ያረጋግጣሉ?
28.
ለሌሎች ሰዎች ክብር መስጠት የየትኛው ማህበረሰብ የተለመደ ባህል ነው?
29.
ፍቅር በምን ላይ ብቻ የተመረኮዘ መሆን የለበትም?
30.
በትምህርት ቤት ውስጥ ለተቸገሩ ጓደኞች ደራሽ መሆን ምንን ማሳየት ነው?