Welcome to your ክፍል 10 አማርኛ ምዕራፍ 5
የሚከተሉትን 30 ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።
1.
"ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን" የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር ምንን ለማስተማር ይውላል?
2.
"በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም" የሚለው አባባል መልዕክቱ ምንድን ነው?
3.
የቅኔ ጥያቄዎች በውስጣቸው ስንት ፍቺዎችን ይይዛሉ?
4.
በቅኔ ውስጥ በግልጽ የሚታየው ወይም የላይኛው ፍቺ ምን ይባላል?
5.
በቅኔ ውስጥ ተደብቆ የሚገኘውና እውነተኛው መልዕክት ምን ተብሎ ይጠራል?
6.
"ዝናቡ ዘነበ ይሞላል ውሃው፣ አወይ ይህን ጊዜ ለተሻገረው" በሚለው ቅኔ ውስጥ ህብረ ቃሉ የትኛው ነው?
7.
ከላይ በቀረበው ቅኔ ("ይህን ጊዜ ለተሻገረው") ውስጥ የወርቅ ፍቺው ምንድን ነው?
8.
ቅኔን ለመፍታት ከሚያስችሉ ዘዴዎች አንዱ የትኛው ነው?
9.
"አስራ ሁለት ውሻ ታስሮ ከደጅሽ፣ አስፈትቼ ገባሁ እኔ ወዳጅሽ" በሚለው ቅኔ ውስጥ ሰሙ ምንድን ነው?
10.
ከላይ ባለው ቅኔ ("አስራ ሁለት ውሻ...") ውስጥ የወርቅ ፍቺው ምንድን ነው?
11.
"ለወትሮው ዳመና ፊቱ እየጠቆረ ይዘንብ ነበረ" በሚለው ግጥም ውስጥ ምን ዓይነት ዘይቤ ተገኝቷል?
12.
"አንገትሽ ብርሌ" በሚለው ግጥም ውስጥ የታየው ዘይቤ ምንድን ነው?
13.
"ውሀ ክፍቱን አድሮ እንዳናጣ ጤና፣ ከዳድኜ እንደሆን ልየው እንደገና" በሚለው ውስጥ ሰሙ ምንድን ነው?
14.
ከላይ በቀረበው ቅኔ ("ከዳድኜ...") ውስጥ የወርቅ ፍቺው ምንድን ነው?
15.
"ሚስቴ በየዓይነቱ ቁርሴን ስትሰጠኝ፣ ቅንጨዋ ናት በጣም የምትጣፍጠኝ" በሚለው ውስጥ ወርቁ ምንድን ነው?
16.
"አዳራሹ ሰፊ በሩ አልጠበባችሁ፣ በተራ በተራ ምነው መግባታችሁ" በሚለው ውስጥ ወርቁ ምንን ይገልጻል?
17.
በአማርኛ ቋንቋ የቃል መጀመሪያ ድምጽ ምን ዓይነት ባህሪ አለው?
18.
"አባይ" የሚለው ቃል ላልቶ ሲነበብ ፍቺው ምንድን ነው?
19.
"አባይ" የሚለው ቃል ጠብቆ ሲነበብ ምን ፍቺ ይሰጣል?
20.
"ጥሬ" የሚለው ቃል ላልቶ ሲነበብ ፍቺው ምንድን ነው?
21.
"ጥሬ" የሚለው ቃል ጠብቆ ሲነበብ የሚሰጠው ፍቺ ምንድን ነው?
22.
"ትናንትና የመጣው ልጅ ዛሬ ተመለሰች" በሚለው ውስጥ የታየው ስህተት ምንድን ነው?
23.
በዓረፍተ ነገር መዋቅር ውስጥ የሚከሰቱ ሰዋስዋዊ ስህተቶች ምን ሊያመጡ ይችላሉ?
24.
"በራ" የሚለው ቃል ላልቶ ሲነበብ ፍቺው ምንድን ነው?
25.
"በራ" የሚለው ቃል ጠብቆ ሲነበብ የሚሰጠው ፍቺ ምንድን ነው?
26.
"ይጣላል" የሚለው ቃል ላልቶ ሲነበብ ፍቺው ምንድን ነው?
27.
"ይጣላል" የሚለው ቃል ጠብቆ ሲነበብ ምን ፍቺ ይኖረዋል?
28.
"ሽፍታ" የሚለው ቃል ላልቶ ሲነበብ ትርጉሙ ምንድን ነው?
29.
"ሽፍታ" የሚለው ቃል ጠብቆ ሲነበብ ፍቺው ምንድን ነው?
30.
"ከፋ" የሚለው ቃል ላልቶ ሲነበብ ፍቺው ምንድን ነው?