ክፍል 10 አማርኛ ምዕራፍ 4

Welcome to your ክፍል 10 አማርኛ ምዕራፍ 4

የሚከተሉትን 30 ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።

1. 
ኢትዮጵያውያን የውጭ ጠላት በመጣ ጊዜ ልዩነቶችን ወደ ጎን በማለት ለሀገር ሰላም ምን ይሆናሉ?

2. 
በልዩነት ውስጥ የሚታይ አንድነት ተምሳሌት ተደርጎ የተጠቀሰው የድል ቀን የትኛው ነው?

3. 
የድርሰት ዋና ዋና ክፍሎች የሚባሉት ስንት ናቸው?

4. 
"ሀረግ መዘዘ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ፍቺው ምንድን ነው?

5. 
"ዓይነ ልም" ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትክክለኛው ፍቺ የትኛው ነው?

6. 
"ሰማይ ጠቀስ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ምንን ይገልጻል?

7. 
"ቅቤ አንጓች" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ማንን ለመግለጽ ይውላል?

8. 
ድርሰት ከመጻፍ በፊት የሚዘጋጅ ረቂቅ ወይም መዋቅር ምን ይባላል?

9. 
በድርሰት ውስጥ ዋናው ሀሳብ በሰፊው የሚተነተንበት ክፍል የትኛው ነው?

10. 
"ሰኔና ሰኞ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ፍቺ ምንድን ነው?

11. 
ነጠላ ዓረፍተ ነገር በውስጡ ስንት ግስ ይይዛል?

12. 
"ትናንት ከባህር ዳር የመጣው ልጅ ዛሬ ተመለሰ" የሚለው ዓረፍተ ነገር በምን ይመደባል?

13. 
ውስብስብ ዓረፍተ ነገር በውስጡ ስንት ግሶችን ይይዛል?

14. 
"አረንጓዴ ሜዳ መንፈስን ያድሳል" የሚለው ዓረፍተ ነገር የትኛው የዓረፍተ ነገር ዓይነት ነው?

15. 
"ቋንቋ በመልመድ እንጂ በመወለድ አይገኝም" የሚለው ዓረፍተ ነገር ምን ዓይነት ነው?

16. 
"አድዋ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለማን ተምሳሌት ነው?" ተብሎ በምንባቡ ተገልጿል?

17. 
በድርሰት ውስጥ የመደምደሚያ ሀሳብ የሚሰፍርበት ክፍል ምን ይባላል?

18. 
"ተራምዶ ደረሰብኝ" በሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ የተቆረጠው አላስፈላጊ ቃል የትኛው ነበር?

19. 
"በሀቅ ላይ የተመሰረተ እውነተኛ አባባል ነው" በሚለው ውስጥ የተደገመው ቃል የትኛው ነው?

20. 
"አርአያ መሆን ሲገባቸው አርአያ አይሆኑም" በሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ የታየው ስህተት ምንድን ነው?

21. 
"መሐመድ በቀዶ ጥገና ትናንት ተመረቀ" በሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ ሙያዊ ቃሉ የትኛው ነው?

22. 
"ቤቶች ሲገነቡ የውሃ ልካቸው ተጠብቆ መሰራት አለበት" በሚለው ውስጥ "የውሃ ልክ" ምን ዓይነት ቃል ነው?

23. 
"ቁንጮ" ለሚለው ቃል መዝገበ ቃላዊ ፍቺው ምንድን ነው?

24. 
"መልቲ" የሚለው ቃል ምንን ይገልጻል?

25. 
"ዳረጎት" ለሚለው ቃል ትክክለኛው ፍቺ የትኛው ነው?

26. 
"ደለዘ" የሚለው ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው?

27. 
"ልጅቷ ከባለቤቷ ጋር በመጣላቷ ጎጆዋ ፈረሰ" በሚለው ዓረፍተ ነገር ውስጥ "ጎጆ" የሚለው ቃል ዓውዳዊ ፍቺው ምንድን ነው?

28. 
"ደራሲው የአንባቢን ልብ የሚነካ ጽሁፍ አቀረበ" በሚለው ውስጥ "ልብ የሚነካ" ማለት ምን ማለት ነው?

29. 
"ወጣቱ ትውልድ የአባቶቹን ታሪክ ያድሳል" በሚለው ውስጥ "ያድሳል" የሚለው ቃል ፍቺ ምንድን ነው?

30. 
"አምበልጋ" የሚለው ቃል ትርጉም ምንድን ነው?

Leave a Reply