Welcome to your ክፍል 10 አማርኛ ምዕራፍ 3
የሚከተሉትን 30 ጥያቄዎች በጥንቃቄ ካነበባችሁ በኋላ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ።
1.
እቴጌ ጣይቱ ንባብንና ጽሕፈትን እንዲሁም ቅኔን የተማሩት የት ነው?
2.
በውስጡ አንድ ግስ የያዘ የዓረፍተ ነገር ዓይነት ምን ይባላል?
3.
ሁለትና ከዚያ በላይ ግሶችን የያዘ ዓረፍተ ነገር ምን ይባላል?
4.
"አረንጓዴ ሜዳ መንፈስን ያድሳል" የሚለው የትኛው የዓረፍተ ነገር ዓይነት ነው?
5.
እቴጌ ጣይቱ ከአድዋ ጦርነት በኋላ ማንን ይንከባከቡ ነበር?
6.
የዓረፍተ ነገር ዓይነቶች ውስጣቸው ከሚይዙት ምን አንጻር ይከፈላሉ?
7.
"ኢትዮጵያውያን ኩሩና ጨዋ ህዝቦች ናቸው" የሚለው ዓረፍተ ነገር የቱ ነው?
8.
"ቋንቋ በመልመድ እንጂ በመወለድ አይገኝም" የሚለው የቱ ነው?
9.
"ችግር ሲመጣ ድንገት ከተፍ ይላል እንጅ ነጋሪት አይጎስምም" የሚለው የቱ ነው?
10.
እቴጌ ጣይቱ በሀገር ግንባታ ላይ ታላቅ ስራ የሰሩት ከማን ጋር ከተጋቡ በኋላ ነው?
11.
ለኢጣሊያን ጋዜጠኞች ለእቴጌ ጣይቱ ምን ያቀርቡ ነበር?
12.
"ልጁ ትናንት ከባህር ዳር መጣ" እና "ልጁ ዛሬ ተመለሰ" የሚሉት ዓረፍተ ነገሮች ሲጣመሩ ምን ይሰጣሉ?
13.
የትኛው ንግሥት ናት ቆራጥነትና አስተዋይነት ተምሳሌት ሆና የምትጠቀሰው?
14.
"አለማየሁ ከክፍለ ሀገር ትናንት በመኪና መጣ" የሚለው የዓረፍተ ነገር ዓይነት የትኛው ነው?
15.
የሥራ ደብዳቤ ከሚይዛቸው ነገሮች አንዱ የቱ ነው?
16.
ክብ ቅርጽ ያለው ማህተም በደብዳቤው የትኛው ክፍል ይቀመጣል?
17.
በአራት ማዕዘን ቅርጽ የሚቀመጠው ማህተም የቱ ነው?
18.
የደብዳቤ መልዕክት ምን አይነት መሆን አለበት?
19.
"ከሰላምታ ጋር!" የሚለው ሐረግ በደብዳቤ ውስጥ ምን ይባላል?
20.
እቴጌ ጣይቱ የትውልድ ስማቸው ማን ነበር?
21.
"ትናንት ከባህር ዳር የመጣው ልጅ ዛሬ ተመለሰ" የሚለው ዓረፍተ ነገር የትኛው ነው?
22.
"በዓለም ላይ ጥቂት ሰነፎች ቢኖሩም ብዙዎቹ ግን ጠንካሮች ናቸው" የሚለው ዓረፍተ ነገር የቱ ነው?
23.
"አፄ ምኒልክ ጣይቱን ሳያማክሩ የሚወስኑት ምንም አይነት ውሳኔ አልነበረም" የሚለው አረፍተ ነገር በምንባቡ መሰረት ምን ያሳያል?
24.
በደብዳቤ ውስጥ "የተቋሙ ልዩ ምልክት" የሚባለው የቱ ነው?
25.
እቴጌ ጣይቱ የትኛው ጦርነት ላይ ከፍተኛ ሚና ነበራቸው?
26.
"ቅጥያ" የሚለው ቃል በየትኛው የዓረፍተ ነገር ስልት ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል?
27.
"፻፲" ለሚለው የግዕዝ ቁጥር የአረብኛው ቁጥር ስንት ነው?
28.
"፳፻" ለሚለው የግዕዝ ቁጥር የአረብኛው ቁጥር ስንት ነው?
29.
"፲፻፻" ለሚለው የግዕዝ ቁጥር የአረብኛው ቁጥር ስንት ነው?
30.
"እንባ ጠባቂ" ማለት ምን ማለት ነው?